የጤና መረጃዎች – Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand. https://www.vejthani.com Get a Medical Check up in Bangkok at Vejthani Hospital Thu, 01 Aug 2024 09:13:09 +0000 et-AM hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.2.2 https://www.vejthani.com/wp-content/uploads/2021/10/favicon.ico የጤና መረጃዎች – Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand. https://www.vejthani.com 32 32 ፔሪፈራል የደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) ልንጠነቀቅበት የሚገባ የተለመደ የጤና ሁኔታ ነው https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8d%94%e1%88%aa%e1%8d%88%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%88%9d-%e1%89%a7%e1%8a%95%e1%89%a7-%e1%89%a0%e1%88%bd%e1%89%b3-peripheral-artery-disease-%e1%88%8d%e1%8a%95%e1%8c%a0%e1%8a%90/ https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8d%94%e1%88%aa%e1%8d%88%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%88%9d-%e1%89%a7%e1%8a%95%e1%89%a7-%e1%89%a0%e1%88%bd%e1%89%b3-peripheral-artery-disease-%e1%88%8d%e1%8a%95%e1%8c%a0%e1%8a%90/#respond Wed, 13 Dec 2023 04:12:53 +0000 https://www.vejthani.com/?p=33285 ስለ ፔሪፌራል የደም ቧንቧ በሽታ (PAD)፣ እንደ ክላዲኬሽን (Claudication) ያሉ ምልክቶችን እና ውጤታማ የአኗኗር ዘይቤ አያያዝን ይማሩ። ቀደም ብሎ ማወቅ ለህክምና አስፈላጊ ነው።

The post ፔሪፈራል የደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) ልንጠነቀቅበት የሚገባ የተለመደ የጤና ሁኔታ ነው appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

የፔሪፈራል ደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) የተለመደ በሽታ ሲሆን የደም ቧንቧዎች መጥበብን ያጠቃልላል ፤ ይህም በእጆች ወይም በእግሮች ላይ የደም ዝውውር እንዲቀንስ ያደርጋል። እጆች ወይም አብዛኛውን ጊዜ እግሮች በቂ ያልሆነ የደም አቅርቦት ይቀበላሉ ፤ ይህም በእግር በሚጓዙበት ጊዜ ወደ እግር ህመም እና ሌሎች ምልክቶች ሊመራ ይችላል።

የፔሪፈራል ደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) አተሮስክለሮሲስ (Atherosclerosis) የሚባል የደም ቧንቧዎች ውስጥ የስብ ክምችቶችን መገንባት ያሳያል። አተሮስክለሮሲስ (Atherosclerosis) የደም ቧንቧዎች መጨናነቅን ያስከትላል ፤ ይህ ደግሞ በእግር እና አልፎ አልፎ በእጆች ላይ የደም ዝውውርን ይቀንሳል።

የደም ቧንቧ በሽታን (Peripheral Artery Disease) ማከም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን ፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብን እና ከማጨስ ወይም ከትንባሆ መቆጠብን ያካትታል።

በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት የደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) ስውር ነው ወይም ምንም ምልክት አይታይበትም። በአንዳንድ ሁኔታዎች ሰዎች በእግር በሚጓዙበት ጊዜ እግሮቻቸው ላይ ህመም ይሰማቸዋል ፤ ይህ ሁኔታ ክላዲኬሽን (Claudication) በመባል ይታወቃል።

የክላዲኬሽን (Claudication) ምልክቶች እንደ ጡንቻ ህመም ወይም በእጆች ወይም በእግሮች ላይ መኮማተር ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚጀምር እና በእረፍት የሚቀል ምልክትን ያካትታል። ህመሙ በዋነኝነት የሚከሰተው በባት አካባቢ ሲሆን መጠኑ  ከቀላል እስከ ከባድ ይለያያል። ከባድ የእግር ህመም ሲኖር እንቅስቃሴ ወይም በተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች መሳተፍ ፈታኝ ሊሆን ይችላል።

ሌሎች የፔሪፈራል ደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ:-

  • ከሌላው ጎን ጋር ሲወዳደር በታችኛው እግር ወይም ባት ላይ ቀዝቃዛ ስሜት
  • በእግር ላይ የመደንዘዝ ስሜት ወይም ድክመት
  • በእግር ወይም በባት ውስጥ የማይገኝ ወይም ደካማ የልብ ምት
  • እንደ መራመድ ወይም ደረጃ መውጣት ያሉ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ተከትሎ በወገብ፣ ጭን ወይም ባት ጡንቻዎች ላይ የሚያሰቃይ ቁርጥማት
  • በእግር ላይ ያለው ቆዳ አንጸባራቂ ሆኖ መታየት
  • በእግር ላይ የቆዳ ቀለም ለውጦች
  • የዘገየ የእግር ጣት ጥፍር እድገት
  • በእግር፣ በእግር ጣቶች ወይም በባት ላይ የማያቋርጡ እና የማይፈወሱ ቁስሎች
  • እንደ መፃፍ ፣ ሹራብ  ወይም የእጅ ሥራዎችን በሚሰሩበት ጊዜ ህመም ፣ ቁርጠት እና ቁርጥማት
  • የብልት መቆም ተግባር
  • የፀጉር መርገፍ ወይም በእግሮች ላይ የፀጉር እድገት መቀነስ

የፔሪፈራል ደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) እየገፋ ሲሄድ በእረፍት ላይ ወይም በሚቀመጡበት ጊዜም ህመም ሊነሳ ይችላል። ይህ ህመም እንቅልፍን ሊያስተጓጉል ይችላል እናም እግሮችን በአልጋ ጠርዝ ላይ በማንጠልጠል ወይም በእግር በመጓዝ ለጊዜው ሊቀንስ ይችላል።

አልፎ አልፎም የደም ስሮች ወይም የእጆች/እግሮች መጎዳት ወይም የጡንቻ ጅማቶች ለውጥ ወይም ለጨረር መጋለጥ የደም ቧንቧ በሽታን (Peripheral Artery Disease) ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ማጨስ ወይም የስኳር በሽታ ካለ ደግሞ የደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) የመያዝ እድልን በእጅጉ ይጨምራል። በተጨማሪም የቤተሰብ ታሪክ፣ የልብ ሕመም ወይም ስትሮክ፣ የደም ግፊት መጨመር፣ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን፣ ከፍተኛ የሆሞሲይስቲን (homocysteine) መጠን የደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) ተጋላጭነትን ይጨምራል፤ በተለይ ከ65 ዓመት ዕድሜ በኋላ ወይም ከመጠን ያለፈ ውፍረት አደጋውን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በመከተል የበሽታውን ምልክቶች መከላከል ይቻላል። ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ አለማጨስን  ፣ የደም ስኳር መጠንን መቆጣጠርን እና ዝቅተኛ ስብ ያላቸውን ምግቦች መጠቀምን ያጠቃልላል። ለትክክለኛው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከሐኪምዎ ጋር በመመካከር አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ ፤ ጤናማ የሰውነት ክብደትን ይጠብቁ እና የደም ግፊትን እና ኮሌስትሮልን ይቆጣጠሩ።

ምልክቶቹን ለመቆጣጠር ከሚወሰዱ መድኃኒቶች በተጨማሪ የፔሪፈራል ደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) በሚከተሉት መንገዶች ሊታከም ይችላል

  • የጠበቡትን ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ለመክፈት የአንጂዎፕላስቲ እና ስቴንት ፕለስመንት (Angioplasty and stent placement) ይከናወናል። ሁለት ዓላማዎች ሲኖሩት የታገዱ ደም ስሮችን ለመመርመር እና ለማከም ወደ ጠባብ የደም ቧንቧ ክፍል ለመሄድ ካቴተር በማስገባት ይከናወናል። አንድ ትንሽ ፊኛ ሲነፋ የተዘጋው የደም ቧንቧ እየሰፋ ይሄዳል፣ ይህም የደም ዝውውርን ያሻሽላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች የደም ቧንቧው ክፍት ሆኖ እንዲቆይ የአንድ ኢምንት የሽቦ መረብ መሳይ ቱቦ (ስተንት) በደም ወሳጅ ቧንቧው ውስጥ ሊቀመጥ ይችላል።
  • የባይፓስ (Bypass) ቀዶ ጥገና የሚከናወነው በተዘጋው የደም ቧንቧ ዙሪያ ተለዋጭ መንገድ በመፍጠር ሲሆን ይህም ከሌላ የሰውነት ክፍል ጤናማ የደም ቧንቧ ወይም በሰው ሰራሽ ምትክ በኩል ነው።
  • ደም ወሳጅ ቧንቧ በደም መርጋት ሲዘጋ የትሮምቦሊቲክ ሕክምና (Thrombolytic therapy) ይመረጣል ፤ የደም መርጋትን  ለማሟሟት የተነደፈው መድሃኒት የተጎዳውን የደም ቧንቧ ለማከም ይረዳል።

ቀደም ብሎ ማወቅ እና እርምጃ ለመውሰድ ፣ የደም ቧንቧ በሽታዎችን (Peripheral Artery Disease) ለመቆጣጠር እና የችግሮቹን ስጋት ለመቀነስ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ህክምና ካልተደረገለት የፔሪፈራል ደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) የግለሰቡን የህይወት ጥራት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ እና ለከባድ የልብና የደም ስር (cardiovascular) ክስተቶች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። ስለዚህ በመጀመሪያዎቹ የሕመም ምልክቶች ላይ የሕክምና እርዳታ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው።

The post ፔሪፈራል የደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) ልንጠነቀቅበት የሚገባ የተለመደ የጤና ሁኔታ ነው appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8d%94%e1%88%aa%e1%8d%88%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%88%9d-%e1%89%a7%e1%8a%95%e1%89%a7-%e1%89%a0%e1%88%bd%e1%89%b3-peripheral-artery-disease-%e1%88%8d%e1%8a%95%e1%8c%a0%e1%8a%90/feed/ 0
የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplantation) ደረጃዎች https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%89%85%e1%8a%92-%e1%8a%95%e1%89%85%e1%88%88-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8b-bone-marrow-transplantation-%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%8c%83%e1%8b%8e/ https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%89%85%e1%8a%92-%e1%8a%95%e1%89%85%e1%88%88-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8b-bone-marrow-transplantation-%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%8c%83%e1%8b%8e/#respond Wed, 13 Dec 2023 04:03:18 +0000 https://www.vejthani.com/?p=33284 ሂሞቶፔይቲክ ስቴም ሴል ትራንስፕላንቴሽን (Stem cell transplantation) ወይም ኤች.ኤስ.ሲ.ቲ (HSCT) በመባል የሚታወቀውን የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplantation) ወይም ቢ.ኤም.ቲ (BMT) ወሳኝ ደረጃዎችን ያስሱ። ለስኬት ቁልፍ የሆኑትን ደረጃዎች በማወቅ የዚህን ውስብስብ ህይወት አድን የሕክምና ሂደት ይረዱ።

The post የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplantation) ደረጃዎች appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplantation) ወይም ቢ.ኤም.ቲ (BMT) ፣ እንዲሁም ሄማቶፖይቲክ ስቴም ሴል ትራንስፕላንቴሽን (Stem cell transplantation) ወይም ኤች.ኤስ.ሲ.ቲ (HSCT) በመባል የሚታወቀው በርካታ ወሳኝ እርምጃዎችን የሚያካትት ውስብስብ የሕክምና ሂደት ነው። ሂደቱ በሚከተሉት ደረጃዎች ሊከፋፈል ይችላል:-

ግምገማ እና ዝግጅት፡- ከቢ.ኤም.ቲ (BMT) በፊት ታካሚዎች ለሂደቱ ብቁነታቸውን ለመወሰን ጥልቅ ግምገማ ይደረግላቸዋል። ይህ ግምገማ አጠቃላይ የጤና እና የበሽታ ደረጃን ለመገምገም የአካል ምርመራዎችን ፣ የደም ምርመራዎችን እና የምስል ጥናቶችን ያካትታል። የጤና አጠባበቅ ቡድኑ እንደ ተስማሚ ለጋሽ መገኘት እና በማገገም ሂደት ውስጥ የታካሚው የድጋፍ ስርዓትን የመሳሰሉ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባል።

የለጋሾች ምርጫ፡- ተስማሚ ለጋሽ ለቢ.ኤም.ቲ (BMT) ስኬት አስፈላጊ ነው። በአሎጄኒክ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት ውስጥ ታካሚዎች እንደራሳቸው ለጋሾች ሆነው ያገለግላሉ፤ አሎጄኔቲክ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት ግን ግንድ ሕዋሶችን ወይም ስቴም ሴሎችን (Stem cells) ተዛማጅነት ወይም ተያያዥነት ከሌለው ለጋሽ ይፈልጋሉ። የለጋሾች ተኳኋኝነት የሚወሰነው በሂውማን ሊውኮሳይት አንቲጂን ኤች.ኤል.ኤ (HLA) መተየብ ነው ፤ ይህ ሙከራ በለጋሽ እና በተቀባዩ ሕዋሳት ላይ ያለውን የፕሮቲን ተኳኋኝነት የሚገመግም ነው።

የማስተካከያ ዘዴ ወይም ኮንዲሽኒንግ ሬጂመን (Conditioning regimen):- ከግንድ ሕዋስ ወይም ስቴም ሴል (Stem cell) ውህደት በፊት ታካሚዎች ከፍተኛ መጠን ያለው የኬሞቴራፒ እና/ወይም የጨረር ሕክምናን የሚያካትት የማስተካከያ ዘዴ ይከተላሉ። ይህ ሂደት የቀሩትን የካንሰር ህዋሶች ለማጥፋት፤ የመወገድ እድልን ለመቀነስ ፣ የመከላከል ብቃትን ለመግታት እና በአጥንት ቅልጥም ውስጥ አዲሶቹ ግንድ ህዋሶች ወይም ስቴም ሴሎች (Stem cells) እንዲያድጉ ለማድረግ ያለመ ነው።

የግንድ ሕዋስ ወይም ስቴም ሴል (Stem cell) ውህደት:- ከኮንዲሽኒንግ ሬጂመን (Conditioning regimen) ስርዓት በኋላ የተሰበሰቡት የስቴም ሴሎች (Stem cells) በማዕከላዊ የደም ስር በካቴተር አማካኝነት ወደ ታካሚው ደም ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋሉ። ሂደቱ ከደም መለገስ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ብዙ ጊዜ ይወስዳል። ከዚያም የስቴም ሴሎች (Stem cells) ወደ መቅኒ ይፈልሳሉ ፤ በመቀጠልም አዲስ የደም ሕዋሶችን ማምረት ይጀምራሉ።

ኢንግራፍትመንት (Engraftment)፡- የተተከሉት ግንድ ሕዋሶች ወይም ስቴም ሴሎች (Stem cells) እራሳቸውን በተቀባዩ መቅኒ ውስጥ አቋቁመው አዲስ የደም ሕዋሶችን ማምረት የሚጀምሩበት ሂደት ነው። ይህ ወሳኝ ደረጃ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከስቴም ሴል (Stem cell) ውህደት በኋላ ከ10 እስከ 28 ቀናት ውስጥ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ታካሚዎች የደም ሕዋሶች ብዛት መጨመርን የመሳሰሉ የኢንግራፍትመንት (Engraftment) ምልክቶች ካሉ በቅርበት ክትትል ይደረግላቸዋል።

ማገገም እና ክትትል፡- ከቢ.ኤም.ቲ (BMT) በኋላ ያለው የማገገሚያ ጊዜ ረጅም እና ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ታካሚዎች በተዳከመ የበሽታ መቋቋም ስርዓታቸው ምክንያት ለኢንፌክሽን እና ለውስብስብ ሁኔታዎች የተጋለጡ ናቸው። ስለዚህ በተለምዶ በተከለለ አካባቢ ውስጥ ይቀመጣሉ እና ተንከባካቢዎችም ጥብቅ የንጽህና እርምጃዎችን መከተል አለባቸው። የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለመቆጣጠር፣ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል እና በአሎጄኔክ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት ውስጥ የ ጂ.ቪ.ኤች.ዲ (GVHD) በሽታ ስጋትን ለመቀነስ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ።

የረዥም ጊዜ ክትትል፡- ከሆስፒታል ከወጡ በኋላ ታካሚዎች ማገገማቸውን ለመከታተል እና እንደ ጂ.ቪ.ኤች.ዲ (GVHD) ወይም እንደ መጀመሪያው በሽታ ተደጋጋሚነት ያሉ ዘግይተው የሚመጡ ችግሮችን ለመገምገም መደበኛ ክትትል ማግኘታቸውን ይቀጥላሉ። ይህ የረዥም ጊዜ ክትትል በታካሚው ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ለብዙ አመታት አልፎ ተርፎም እድሜ ልክ ሊቆይ ይችላል።

የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ውስብስብ እና ባለብዙ ደረጃ ሂደት ሲሆን በታካሚው፣ በጤና አጠባበቅ ቡድን እና በለጋሽ መካከል ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ እና ቅንጅትን የሚጠይቅ ነው። ቢ.ኤም.ቲ (BMT) ለተለያዩ ሁኔታዎች ህይወት አድን ህክምና ሊሆን ቢችልም ፤ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ይይዛል እና ረጅም የማገገሚያ ጊዜን ይፈልጋል፤ ስለዚህ ጥልቅ ግምገማ እና ክትትል ለስኬቱ ወሳኝነት ያኖረዋል።

The post የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplantation) ደረጃዎች appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%89%85%e1%8a%92-%e1%8a%95%e1%89%85%e1%88%88-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8b-bone-marrow-transplantation-%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%8c%83%e1%8b%8e/feed/ 0
3 መደበኛ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴዎች https://www.vejthani.com/am/2023/12/3-%e1%88%98%e1%8b%b0%e1%89%a0%e1%8a%9b-%e1%8b%a8%e1%8c%a1%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%88%98%e1%88%ab-%e1%8b%98%e1%8b%b4%e1%8b%8e%e1%89%bd-breast-cancer-screeni/ https://www.vejthani.com/am/2023/12/3-%e1%88%98%e1%8b%b0%e1%89%a0%e1%8a%9b-%e1%8b%a8%e1%8c%a1%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%88%98%e1%88%ab-%e1%8b%98%e1%8b%b4%e1%8b%8e%e1%89%bd-breast-cancer-screeni/#respond Mon, 04 Dec 2023 08:40:14 +0000 https://www.vejthani.com/?p=33074 በጡት ካንሰር (Breast Cancer) የግንዛቤ ወር ውስጥ እራስዎን ያበረታቱ። ማሞግራም (Mammogram) እና ባዮፕሲዎችን ጨምሮ ስለ ውጤታማ የጡት ካንሰር ምርመራ

The post 3 መደበኛ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴዎች appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

ጥቅምት ወር የጡት ካንሰር (Breast Cancer)ግንዛቤን ያከብራል። በታይላንድ ውስጥ ሴቶች ላይ የጡት ካንሰር (Breast Cancer)በጣም የተስፋፋ የካንሰር አይነት ሲሆን ከ 100,000 ሴቶች ውስጥ 28.6 የሚሆኑት በበሽታው ይያዛሉ።

የጡት ካንሰር (Breast Cancer)በመስፋፋቱ ምክንያት ከካንሰር ጋር በተያያዙ በሽታዎች ከፍተኛ የሞት መጠን ካላቸው መካከል ይጠቀሳል። የጡት ካንሰር (Breast Cancer) ምርመራ በማድረግ ቀደም ብሎ ማግኘቱ ዘላቂ የመፈወስ እድልን ስለሚያሳድግ የሞት መጠንን ለመቀነስ ጠቃሚ መሳሪያ ነው።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የጡት ስፔሻሊስት እና ኦንኮፕላስቲክ የጡት ቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ፒያሳክ ታሃራቫኒች መደበኛው የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast Cancer Screening) የሚከተሉትን ሶስት ደረጃዎች ያካተተ ነው ብለዋል:-

  1. በሐኪም የሚወሰድ የታካሚ የህክምና ታሪክ እና በጡት ቀዶ ጥገና ሐኪም የሚደረግ የጡት ምርመራ: ከ 40 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች በአመት አንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast Cancer Screening) እንዲያደርጉ ይመከራሉ።
  2. ማሞግራም (Mammogram) እና አልትራሳውንድ፡ በተለምዶ የምርመራ ውጤቶቹ በቢራድስ (BIRADS) ነጥብ (የጡት ምስል ቀረጻ እና ዳታ ሲስተም) ይታያሉ። ቁጥሮቹ ከ0-6 ይደርሳሉ:-
    • BIRADS 0 ማለት የተገኘው መረጃ ለምርመራ በቂ አይደለም ማለት ነው ፤ተጨማሪ ምርመራዎች ያስፈልጋሉ።
    • BIRADS 1 እና 2 ማለት ምንም አይነት የጡት ካንሰር (Breast Cancer) ስጋት አልተገኘም ማለት ነው ፤ ታካሚዎች ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶችን ለመፈለግ በዓመት አንድ ጊዜ የክትትል ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ።
    • BIRADS 3 ማለት የጡት ካንሰር (Breast Cancer) አደጋ መገኘቱን ያመላክታል ፤ ነገር ግን በሽታው የመከሰት እድሉ ከ 2% ያነሰ ነው ፤ በየ 6 ወሩ የክትትል ምርመራ እንዲደረግ ይመከራል።
    • BIRADS 4 ማለት የካንሰር አደጋ ከ2-95% እድል ተገኝቷል ማለት ነው ፤ ለማረጋገጫ ባዮፕሲ ይመከራል።
    • BIRADS 5 ማለት የካንሰር አደጋ ከ95 በመቶ በላይ እድል ሲኖረው የተገኘ ነው ማለት ነው ፤ ለማረጋገጫ ባዮፕሲ ይመከራል።
    • BIRADS 6 ማለት በባዮፕሲ ውጤቱ የተሰበሰበው ህዋስ ካንሰር እንደሆነ ያሳያል።
  1. ባዮፕሲ የጡት ካንሰርን (Breast Cancer) ለመመርመር እና ለማረጋገጥ አስፈላጊ ሂደት ነው። ይህ ዘዴ ጥቅም ላይ የሚውለው አንድ ታካሚ 3D ማሞግራም (Mammogram) እንዲሁም አልትራሳውንድ ሲደረግ እና ውጤቶቹ የ BIRADS ከ 4 ወይም 5 በላይ ሲያሳዩ ነው። ሶስት ዓይነት ባዮፕሲዎች ሲኖሩ እንደሚከተለው ናቸው:-
    • ፋይን ኒድል አስፓየሬሽን (Fine Needle Aspiration) ወይም ኤፍ.ኤን.ኤ (FNA)፡- ባለ 22-መለኪያ (ቦዶ) መርፌ ወደ እብጠቱ ውስጥ በማስገባት እና ከተጠረጠረው አካባቢ ህዋሶችን በማውጣት የካንሰር ህዋሳትን ለማግኘት ይረዳል። የዚህ ዘዴ ጠቀሜታው ከ1-2 ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚወስደው። የBIRADS ውጤታቸው 5 ለሆነ ወይም ለጡት ካንሰር (Breast Cancer) ከፍተኛ ተጋላጭነት ላለባቸው ሴቶች ተስማሚ ነው። የምርመራው ውጤት በሴሉላር ፓቶሎጂስት መተርጎም አለበት።
    • ኮር ኒድል ባዮፕሲ (Core Needle Biopsy) ፡ አንድ ትልቅ መርፌ በተጠረጠረው እብጠት ውስጥ ተመርቶ ከ 3-4 ህዋሶች ይቆርጣል። የዚህ ዓይነቱ ባዮፕሲ የሕዋስ አወቃቀሮችን እና ጉዳቶችን በበለጠ ዝርዝር ማየት ስለሚያስችል ለሕዋስ ምልከታ የበለጠ ትክክለኛነትን ይሰጣል። ኮር ኒድል ባዮፕሲ ወደ 30 ደቂቃ አካባቢ ሲወስድ ከሂደቱ በፊት የማደንዘዣ መርፌ ይሰጣል።
    • ቫክዩም አሲስት (Vacuum Assist) ፡ ትልቅ መርፌ ወደ እብጠቱ ይገባል። መርፌው ህዋሶችን በመምጠጥ በተደጋጋሚ እየቆራረጠ ወደ ቫክዩም ያስገባል። ይህም የሚጠቅመው ሙሉውን እብጠት ለማስወገድ ያስችላል። ሆኖም ግን ሙሉውን እብጠት ማስወገድ የሚመከረው ዶክተሩ እብጠቱ ካንሰር አለመሆኑን ሲተማመን ብቻ ነው። መርፌው ከመግባቱ በፊት አካባቢው ላይ ማደንዘዣ ይደረጋል። እንደ ቁስለቱ ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ሂደቱ ወደ 40 ደቂቃዎች ያህል ይወስዳል።

ትክክለኛው የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast Cancer Screening) የጡት ቀዶ ጥገና ሃኪም በማማከር እና ለበለጠ ትክክለኛ የምርመራ ውጤት ከማሞግራም (Mammogram) እና ከአልትራሳውንድ ጋር የታገዘ ጡት ምርመራን ያካትታል።

የምርመራ ውጤቶቹ BIRADS 4 ወይም 5 ነጥብ ከሆኑ ለታካሚው ከቀዶ ጥገናው በፊት ውጤታማ የሆነ ህክምና ለማቀድ ባዮፕሲ መደረግ ይኖርበታል ፤ ይህም ለበሽታው እና ላለበት የካንሰር ደረጃ በጣም ተስማሚ መሆን አለበት።

“ቀዶ ጥገና ሲባል ብዙ ታካሚዎች ሙሉውን ጡት ማስወገድ ያሳስባቸዋል። ግን እውነታው ለአንዳንድ ታካሚዎች በተለይም የመጀመሪያ ደረጃ ጡት ካንሰር (Breast Cancer)ላለባቸው ፤ እብጠቱ ትንሽ ከሆነ አጠቃላይ ጡትን ማስወገድ አያስፈልግም። በአሁኑ ጊዜ የጡት ማቆያ ቴክኒክ ቀዶ ጥገና አለ ፤ ነገር ግን ጡቱ ከሌላኛው ጋር ተመሳሳይነት ያለው መዋቅር እና መልክ እንዲኖረው ይጠይቃል። ሙሉውን ጡት እንዲወገድ ለሚያስፈልገው ሁኔታ ማስቴክቶሚም አለ ፤ ነገር ግን የጡት ቆዳን፣ የጡት ጫፍንና የአካባቢውን ቆዳ ሳይነካ እንዳለ ይጠብቃል። የማስቴክቶሚ ቀዶ ጥገና ከተደረገ በኋላ የጡት መልሶ መገንባት የሴትን ማንነት እና መተማመንን ለመጠበቅ ሊደረግ ይችላል።”

ዶክተር ፒያሳክ

ለበለጠ መረጃ እባክዎን የካንሰር ማዕከልን፣ በቬጅታኒ ሆስፒታል ያነጋግሩ።
ይደውሉ፡ 02-734-0000 Ext. 5500
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66) 0- 90-907-2560
ኢሜል፡ ethiopian@vejthani.com

The post 3 መደበኛ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴዎች appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/12/3-%e1%88%98%e1%8b%b0%e1%89%a0%e1%8a%9b-%e1%8b%a8%e1%8c%a1%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%88%98%e1%88%ab-%e1%8b%98%e1%8b%b4%e1%8b%8e%e1%89%bd-breast-cancer-screeni/feed/ 0
የሽባነት (paralysis) ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል (paresis) ስጋትን ለመቀነስ አይስኬሚክ ስትሮክን (Stroke)ወዲያውኑ ያክሙ https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8b%a8%e1%88%bd%e1%89%a3%e1%8a%90%e1%89%b5-paralysis-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%89%80%e1%88%b3%e1%89%80%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%88%98%e1%89%bb%e1%88%8d-paresis/ https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8b%a8%e1%88%bd%e1%89%a3%e1%8a%90%e1%89%b5-paralysis-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%89%80%e1%88%b3%e1%89%80%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%88%98%e1%89%bb%e1%88%8d-paresis/#respond Mon, 04 Dec 2023 08:23:51 +0000 https://www.vejthani.com/?p=33073 የሽባነት (paralysis) ስጋትን ለመቀነስ አይስኬሚክ ስትሮክን (Ischaemic stroke) በአፋጣኝ ያክሙ። ስለአደጋ መንስኤዎች፣ ምርመራ እና ውጤታማ ህክምናዎች ይወቁ። ዶክተር ፖንግሳኮርን ለጤናማ ህይወት የመከላከያ ስልቶችን ይመክራሉ።

The post የሽባነት (paralysis) ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል (paresis) ስጋትን ለመቀነስ አይስኬሚክ ስትሮክን (Stroke)ወዲያውኑ ያክሙ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

ሴሬብሮቫስኩላር በሽታ (Cerebrovascular Disease) ወይም ስትሮክ (Stroke) ለሽባነት (paralysis) ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል (paresis) ዋና መንስኤዎች ናቸው። በሽታው ያለባቸው ሰዎች በድንገተኛ ጥቃቶች የሚሰቃዩ ሲሆን የሕክምና ክትትል በወቅቱ ማግኘት የፈውስ እድልን ይጨምራል።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የነርቭ ቀዶ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ፖንግሳኮርን ፖንግሳፓስ እንዳስረዱት ሴሬብሮቫስኩላር በሽታ (Cerebrovascular Disease) ወይም ስትሮክ (Stroke) የሚከሰተው በደም ወሳጅ ቧንቧዎች መዘጋት ወይም በአንጎል ውስጥ ያሉ የደም ስሮች መጥበብ ወይም መቀደድ ሳቢያ ወደ አንጎል የደም ዝውውር እንዲስተጓጎል በማድረግ የተወሰኑ ምልክቶች እንዲታዩ ያደርጋል ፤ ይህም እንደ የፊት ሽባ መሆን፣ ብዥ ያለ እይታ፣ ድርብ እይታ፣ ድክመት፣ መደንዘዝ ወይም በአንድ የአካል ክፍል ላይ የሚከሰት ሽባነት (paralysis) ፣ የደበዘዘ ንግግር ወይም መናገር አለመቻልን ያካትታል። የስትሮክ (Stroke) በሽታ የሚከሰተው በመካከለኛ እና በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ነው ፤ ነገር ግን የደም ስሮቻቸው በእድሜ መበላሸታቸው ምክንያት ሁኔታው ​​በአረጋውያን ላይ በብዛት ይታያል።

የስትሮክ (Stroke) ስጋት ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  1. የደም ግፊት፡- ረዘም ላለ ጊዜ ከ140/90 ሚሜ ኤችጂ በላይ የደም ግፊት ያላቸው ሰዎች የደም ስሮቻቸው ከአማካይ በበለጠ ፍጥነት ይበላሻሉ። ይህ የደም ቧንቧ መዘጋት ፣ መጥበብ (ስቴኖሲስ) ወይም የደም ስሮች መቀደድ አደጋን ከፍ ያደርገዋል።
  2. የስኳር በሽታ፡- የደም ቧንቧ መበላሸት ያስከትላል፣ ይህም ከስትሮክ (Stroke) ጋር የተገናኙ ችግሮችን ይጨምራል።
  3. የልብ ሕመም፡- መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት (ሀርት አሪዝሚያ) ፣ የሴፕታል እክል እና አይስኬሚክ ካርዲዮሚዮፓቲ ያካትታል ፤ እነዚህም በአንጎል ውስጥ የደም መርጋትን የሚያስከትሉ ሲሆን ይህም የሚፈጠረው ወደ ደም ስሮች እና ደም ወሳጅ ቧንቧዎች በመዛመት እና በመዘጋት ነው
  4. ሃይፐርሊፒዲሚያ፡- የሚያቃጥል ምላሽን በማምጣት እና በደም ወሳጅ ቧንቧ ግድግዳዎች ላይ የስብ ክምችቶችን በመፍጠር ደም ስሮች እንዲበላሹ በማድረግ የመዘጋት ፣ መጥበብ (ስቴኖሲስ) ወይም መቀደድ አደጋን ያስከትላል።
  5. ማጨስ፡- ሲጋራ በአንጎል ውስጥ የደም ስሮች መበላሸትን የሚያፋጥኑ ኬሚካሎች አሉት። “ብዙ ባጨሱ ቁጥር ስትሮክ (Stroke) ይጨምራል” እንደሚባለው አጫሾች ከማያጨሱ ሰዎች ይልቅ ለስትሮክ የመጋለጥ እድላቸው በስድስት እጥፍ ከፍ ያለ ነው።
  6. አልኮልን በብዛት መጠጣት፡- የልብ አሰራር ብልሽትን ያስከትላል ፤ ይህም ወደ አዕምሮ ደም ስሮች እንዲሰራጭ ልማሞ እና የደም መርጋት በማስከተል እንዲዘጋ ያደርጋል።
  7. ከመጠን በላይ መወፈር እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የደም ስሮችን፣ የደም ቧንቧዎችን እና የልብን ውጤታማነት ይጨምራል። ስትሮክን (Stroke) ለመከላከል እና የልብ ስራን በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራ ያደርጋል ፤ ይህም ለስትሮክ (Stroke) የመጋለጥ እድልን በእጅጉ ይቀንሳል።

ስትሮክ (Stroke) በሲቲ ስካን፣ ኤምአርአይ እና ኤምአርኤ፣ ትራንስክራኒያል ዶፕለር ወይም ቲሲዲ (TCD) እና ካሮቲድ ዶፕለር ከሌሎች ተጨማሪ ዘዴዎች ጋር ሊታወቅ ይችላል። ትክክለኛ ምርመራ ዶክተሮች ውጤታማ የሆነ የመከላከያ እና የሕክምና እቅድ እንዲያወጡ ይረዳል።

ስትሮክን (Stroke) ለማከም ያለው መርህ የአንጎል ሴሎችን ረጅም ዕድሜ እና ህልውና መጠበቅ ነው። በደም ስሮች ውስጥ በቂ እና ያልተቋረጠ የደም ዝውውር የአንጎል ህዋሶች በፍጥነት እንዲያገግሙ ያስችላቸዋል ፤ ይህም ታካሚዎች ወደ መደበኛ የጤና ሁኔታቸው እንዲመለሱ ያደርጋል። ዶክተሩ በስትሮክ (Stroke) ሕክምና የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ክሊኒካዊ ግምገማ ይጀምራል።  ፀረ-ደም መርጋት መድኃኒቶችን ያለ ገደብ እንደ ሕክምና ለመውሰድ ጠቋሚዎች ካሉ ፤ ምልክቶቹ ከተከሰቱ በኋላ በ 4.5 ሰዓታት ውስጥ ዶክተሩ ወደ አንጎል የደም አቅርቦትን የሚዘጋውን የደም መርጋት ለማስቆም መድኃኒቶቹን ያዝዛል። ነገር ግን በትልልቅ የደም ስሮች ውስጥ መዘጋት ካለ ሐኪሙ በሜካኒካል ትሮምቤክቶሚ ያክማል። አሰራሩ የደም መርጋትን ለማስወገድ ብሽሽት ላይ ትንሽ ቀዳዳ በመፍጠር በዛ ውስጥ አልፎ ወደ አንጎል በሚያመሩት ደም ስሮች ውስጥ ካቴተር ማስገባትን ያካትታል። ሜካኒካል ትሮምቤክቶሚ በፍጥነት የሚከናወን የኢንዶቫስኩላር ቴክኒክ ሲሆን ይህም የአንጎል ስራን በመጠበቅ አነስተኛ ጉዳት ያስከትላል።

ታካሚዎች በስትሮክ (Stroke) በሽታ የመያዝ እድልን ለመቀነስ በሚከተሉት መንገዶች  ከአደጋ መንስኤዎች መራቅ አለባቸው፡-

  • የደም ግፊትን በመደበኛ ክልል ውስጥ ማቆየት
  • በኮሌስትሮል እና ቅባቶች የበለፀጉ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ
  • ማጨስን እና የአልኮል መጠጦችን ማስወገድ
  • የስኳር ህመምተኞች የስኳር መጠን መቆጣጠር
  • የሰውነት ክብደትን ጤናማ በሆነ ክልል ውስጥ ማቆየት
  • ተጨማሪ አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ
  • አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

“ስትሮክ (Stroke) በታካሚዎች የህይወት ጥራት እና በአካባቢያቸው ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ስለዚህ የራሳቸውን ጤና ከመጠበቅ በተጨማሪ ሌላው አስፈላጊ ነገር ያልተለመዱ ምልክቶችን መከታተል ነው። ምክንያቱም በሽታው ቀደም ብሎ ከታወቀ ማከም ይቻላል ፤ ይህም ሽባነትን (paralysis) ሊቀንስ ይችላል። “ ዶክተር ፖንግሳኮርን

The post የሽባነት (paralysis) ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል (paresis) ስጋትን ለመቀነስ አይስኬሚክ ስትሮክን (Stroke)ወዲያውኑ ያክሙ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/12/%e1%8b%a8%e1%88%bd%e1%89%a3%e1%8a%90%e1%89%b5-paralysis-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%89%80%e1%88%b3%e1%89%80%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%88%98%e1%89%bb%e1%88%8d-paresis/feed/ 0
የአከርካሪ አጥንት መጥበብ ወይም ስቴኖሲስ (Spinal Stenosis) – በአረጋውያን ላይ የተለመደ በሽታ https://www.vejthani.com/am/2023/11/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8a%a8%e1%88%ad%e1%8a%ab%e1%88%aa-%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8c%a5%e1%89%a0%e1%89%a5-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%8a%96%e1%88%b2/ https://www.vejthani.com/am/2023/11/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8a%a8%e1%88%ad%e1%8a%ab%e1%88%aa-%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8c%a5%e1%89%a0%e1%89%a5-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%8a%96%e1%88%b2/#respond Mon, 27 Nov 2023 09:53:10 +0000 https://www.vejthani.com/?p=32894 በአረጋውያን ላይ በአከርካሪ አጥንት መጥበብ (Spinal Stenosis) እና በጀርባ ህመም (Back pain) መካከል ያለውን ግንኙነት ይወቁ። ስለ ምልክቶቹ እና ውጤታማ ለሆነ ህክምና ወቅታዊ ምርመራ አስፈላጊነት ይወቁ። በኤክስሬይ እና በኤምአርአይ የታገዙ ትክክለኛ ግምገማዎች ለማድረግ ልዩ ባለሙያዎችን ያማክሩ።

The post የአከርካሪ አጥንት መጥበብ ወይም ስቴኖሲስ (Spinal Stenosis) – በአረጋውያን ላይ የተለመደ በሽታ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

የአከርካሪ አጥንት ስቴኖሲስ (Spinal Stenosis) ወይም የአከርካሪ አጥንት ቦይ መጥበብ በአረጋውያን ላይ በብዛት የሚገኝ በሽታ ነው። በሽታው በአከርካሪ አጥንት አካባቢ ውስጥ የሚገኙትን ዲስኮች ፣ ጅማቶች እና መገጣጠሚያዎችን የሚጎዳው በአከርካሪ አጥንት መበላሸት ምክንያት ነው።

የአከርካሪ አጥንት ቦይ ከእድሜ ጋር እየጠበበ ይሄዳል ፤ ምናልባትም ነርቮችን እስከሚጨምቅበት ደረጃ ይደርሳል። የነርቭ መጨናነቅ ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱን ሊያስከትል ይችላል:-

  • የዳሌ እና የወገብ ህመም
  • ከረጅም የእግር ጉዞ በኋላ የሚባባስ የእግር ህመም
  • ወደ ኋላ በሚታጠፍ ጊዜ የሚባባስ እና በእረፍት ጊዜ ወይም ወገብን ወደ ፊት በማጠፍ የሚቀንስ የጀርባ ህመም (Back pain)

የጀርባ ህመም (Back pain) ላጋጠማቸው እና ባልታወቀ ምክንያት የመራመድ ችግር ላጋጠማቸው አረጋውያን ታካሚዎች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ለእያንዳንዱ ታካሚ ልዩ ባለሙያተኛን በማማከር ለምርመራ እንደ ኤክስሬይ እና ኤምአርአይ ያሉ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ለበለጠ መረጃ እባክዎን የአከርካሪ አጥንት ማዕከልን፣ በቬጅታኒ ሆስፒታል ያነጋግሩ።

ይደውሉ፡ 02-734-0000 Ext. 5500
የአማርኛ ስልክ መስመር:  (+66) 0- 90-907-2560
ኢሜል፡ ethiopian@vejthani.com

The post የአከርካሪ አጥንት መጥበብ ወይም ስቴኖሲስ (Spinal Stenosis) – በአረጋውያን ላይ የተለመደ በሽታ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/11/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8a%a8%e1%88%ad%e1%8a%ab%e1%88%aa-%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8c%a5%e1%89%a0%e1%89%a5-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%8a%96%e1%88%b2/feed/ 0
የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር፡- ቀደም ብሎ መለየት ወደ ፈጣን ህክምና ይመራል https://www.vejthani.com/am/2023/09/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%8e%e1%88%ac%e1%8a%ad%e1%89%b3%e1%88%8d-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad%e1%8d%a1-%e1%89%80%e1%8b%b0/ https://www.vejthani.com/am/2023/09/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%8e%e1%88%ac%e1%8a%ad%e1%89%b3%e1%88%8d-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad%e1%8d%a1-%e1%89%80%e1%8b%b0/#respond Fri, 08 Sep 2023 07:36:12 +0000 https://www.vejthani.com/?p=31693 የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር ከሁሉም የካንሰር አይነቶች 4ኛው በብዛት ከሚገኝ ካንሰር ነው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሞት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ምክንያቱም "ኮሎኖስኮፒ" በተባለ የማጣሪያ ምርመራ በመገኘቱ ምክንያት ነው።

The post የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር፡- ቀደም ብሎ መለየት ወደ ፈጣን ህክምና ይመራል appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር ከሁሉም የካንሰር አይነቶች 4ኛው በብዛት ከሚገኝ ካንሰር ነው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሞት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ምክንያቱም “ኮሎኖስኮፒ” በተባለ የማጣሪያ ምርመራ በመገኘቱ ምክንያት ነው።

የኮሎሬክታል ካንሰር የሚከሰተው በአንጀት (ኮሎን) ውስጥ ትንንሽ ዕጢ ወይም ፖሊፕ በመኖሩ ምክንያት ነው። በመነሻ ደረጃ ላይ ምንም ምልክቶች አይታዩም ፤ ነገር ግን ፖሊፖች ሲያድጉ እና ወደ ካንሰር ሲቀየሩ ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ። ምልክቶቹ በሰገራ ውስጥ ደም የተቀላቀለ ንፍጥ፣ የሰገራ ማነስ፣ ተለዋዋጭ የሆድ ድርቀት እና ተቅማጥ፣ የሆድ ድርቀት መጨመር፣ የሆድ መነፋት ወይም በሆድ ውስጥ የሚታይ እብጠት ይገኙበታል።

ስለሆነም ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በየጊዜው የኮሎንኮፒ ምርመራ ካደረጉ በሽታው ቀደም ብሎ ስለሚታወቅ ታማሚዎቹ አፋጣኝ ሕክምና እንዲያገኙ ያስችላል።

ለኮሎሬክታል ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች ኮሎንኮስኮፒን በሚከተለው መልኩ እንዲወስዱ ይመከራሉ:-

  • ከ 50 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች በየ 3-5 ዓመቱ ኮሎንኮስኮፒ እንዲያደርጉ ይመከራሉ
  • የአንጀት እንቅስቃሴ ላይ ችግር ያለባቸው ፤ እንደ ሆድ ድርቀት ወይም ተደጋጋሚ ተቅማጥ ወይም ተለዋዋጭ የሆድ ድርቀት እና ተቅማጥ
  • ደም ያለበት ሰገራ ፣ ደማቅ ቀይ ወይም ጥቁር ቀለም ያለው እና ያልተለመደ ሽታ ሊኖረው ይችላል
  • ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ ዕጢዎች ወይም ፖሊፕች ሰገራ በማማጥ ጊዜ ሊቀደዱ ይችላሉ ፤ ይህም የደም መፍሰስ ሊኖረው ይችላል
  • የሆድ መወጠር ፣ መነፋት እና ህመም
  • የሆድ እብጠት ፣ የክብደት መቀነስ ፣ የቆዳ መገርጣት እና ድካም

ለበለጠ መረጃ፡-እባኮትን የላይፍ ካንሰር ማዕከልን በቬጅታኒ ሆስፒታል ያነጋግሩ;- ስልክ. 02-734-0000
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66) 90-907-2560

The post የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር፡- ቀደም ብሎ መለየት ወደ ፈጣን ህክምና ይመራል appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/09/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%8e%e1%88%ac%e1%8a%ad%e1%89%b3%e1%88%8d-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad%e1%8d%a1-%e1%89%80%e1%8b%b0/feed/ 0
የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት (ስቴም ሴል) እንዴት ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል https://www.vejthani.com/am/2023/09/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%89%85%e1%8a%92-%e1%8a%95%e1%89%85%e1%88%88-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8b-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%8a%95%e1%88%b5/ https://www.vejthani.com/am/2023/09/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%89%85%e1%8a%92-%e1%8a%95%e1%89%85%e1%88%88-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8b-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%8a%95%e1%88%b5/#respond Thu, 07 Sep 2023 08:44:50 +0000 https://www.vejthani.com/?p=31643 የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ቢኤምቲ (BMT) ፣ እንዲሁም ሄማቶፖይቲክ ስቴም ሴል ትራንስፕላንት ወይም ኤች.ኤስ.ሲ.ቲ (HSCT) በመባል የሚታወቀው፣ የተጎዳ ወይም የታመመ መቅኒ በጤናማ ግንድ ሕዋስ

The post የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት (ስቴም ሴል) እንዴት ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ቢኤምቲ (BMT) ፣ እንዲሁም ሄማቶፖይቲክ ስቴም ሴል ትራንስፕላንት ወይም ኤች.ኤስ.ሲ.ቲ (HSCT) በመባል የሚታወቀው፣ የተጎዳ ወይም የታመመ መቅኒ በጤናማ ግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) መተካትን የሚያካትት የህክምና ሂደት ነው። ይህ ሕክምና የተለያየ የደም ሕመም፣ ካንሰር እና የበሽታ መከላከል ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ሕይወት አድን ሊሆን ይችላል። እዚህ በቢኤምቲ ሊታከሙ ስለሚችሉ አንዳንድ ሁኔታዎች ዝርዝር መግለጫ እናቀርባለን።

የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት ለህክምና የሚውለው፡-

  • የአጥንት መቅኒ ወይም ግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ተጎድተው ጤናማ የደም ሴሎችን ማምረት ካልቻሉ
  • የአጥንት መቅኒ ወይም የደም ሕዋሶች ጤናማ ካልሆኑ ወይም ሕመምተኞች ጤናማ የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ለመተካት የሚያስገድድ ሕመም ሲኖራቸው
  • ከፍተኛ መጠን ያለው ኬሞቴራፒ ወይም ጨረራ ከተወሰደ በኋላ እና ሁለቱንም የካንሰር ሕዋሳት እና ጤናማ ሕዋሶች ላይ ተፅዕኖ ይኖራል። ይህ ደግሞ የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት ያስፈልገዋል።

የግንድ ሕዋሶች ወይም ስቴም ሴሎች በአጥንት መቅኒ ውስጥ እና በአጥንት ለስላሳ ሕብረ ሕዋሳት እንዲሁም በእምብርት ገመድ ውስጥ ያድጋሉ። ለተወሰነ ጊዜ ካደጉ በኋላም ወደሚከተሉት ይለወጣሉ:-

  • ፕሌትሌትስ የደም መርጋትን ለመከላከል
  • ቀይ የደም ሴሎች በደም ውስጥ ለንጹህ ኦክስጅን
  • ነጭ የደም ሴሎች የውጭ በሽታዎችን ለመዋጋት የበሽታ መከላከያ እድገት

የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ሕክምና እንዴት ይሠራል?

ሁለት ዓይነት ንቅለ ተከላዎች ሲኖሩ ለታካሚው የትኛው የተሻለ እንደሆነ ሐኪሙ ይወስናል።

  • አውቶሎገስ (AUTO) ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት

ይህ ከአጥንት መቅኒ ወይም ከደም የተገኘ ጤናማ የግንድ ሕዋሶች ወይም የስቴም ሴሎች ስብስብ ነው። ከዚያም ዶክተሮች በማቀዝቀዝ በጥንቃቄ ያስቀምጧቸዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው የኬሞቴራፒ ሕክምና ከተደረገ በኋላ ሕዋሶቹ በደም ስር (አይቪ) በኩል ደም ውስጥ በመግባት ወደ መቅኒ ይመለሳሉ። ይህም የአጥንት ቅልጥሞች ጤናማ የደም ሕዋሶችን እንደገና እንዲያመርቱ እና በሰውነት ውስጥ ያለውን በሽታ የመከላከል አቅምን በቡድን እንዲያሰባስቡ ያስችላቸዋል።

  • አሎጄኒክ ወይም አሎ (ALLO) ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት

ይህ የሚደረገው ከለጋሾች ጤናማ የአጥንት መቅኒ በመውሰድ ነው። ደም ከመውሰዱ በፊት የለጋሽ አጥንት መቅኒ ከታካሚው መቅኒ ጋር የሚጣጣም መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ካልሆነ የታካሚው አካል የተተከሉትን ሕዋሶች ካላወቀ ውድቅ ይሆናል። የቤተሰብ አባል ለጋሽ ለመሆን ከሁሉ የተሻለ ምርጫ መሆን አለበት። አሎ ከመውሰዱ በፊት ኬሞቴራፒ ፣ ራዲዮቴራፒ ወይም የሁለቱ ሕክምናዎች ጥምረት የድሮውን ግንድ ሕዋሶች ወይም ስቴም ሴሎች በአዲስ ለመተካት አስቀድሞ መሰጠት አለበት።

የእምብርት ገመድ ደም ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ከአሎጄኒክ ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ጋር ይመስላል። ነገር ግን ልዩ የሚያደርገው ነገር የሚለገሰው ከህፃን እምብርት መሆኑ ነው። ስለዚህ ከግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ጋር ከመመዋሃዱ በፊት የኬሞቴራፒ ሕክምናን የመቀበል እድሉ አነስተኛ ነው። ታካሚው ተገቢውን ለጋሽ ማግኘት በማይችልበት ጊዜ ዶክተሩ ይህንን የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ለህክምና መጠቀም ይኖርበታል። ነገር ግን የተለገሱ ሕዋሶች ከታካሚው አካል ውጭ ስለሚወሰዱ ለችግር የመጋለጥ ስጋት ምንጊዜም ይኖራል።

ስጋቶቹ ምንድን ናቸው?

ከአውቶሎገስ ወይም ከአሎጄኒክ ንቅለ ተከላ በፊት ታካሚው አስቀድሞ ከፍተኛ መጠን ያለው የኬሞቴራፒ ሕክምና ያስፈልገዋል። ስለዚህ እሱ ወይም እሷ በሚከተሉት የኬሞቴራፒ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊሰቃዩ ይችላሉ:-

  • ማቅለሽለሽ
  • ከባድ ኢንፌክሽኖች
  • ማስታወክ
  • ድካም
  • የደም መፍሰስ

በእነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች መሰቃየት ለታካሚው ጥሩ ባይሆንም ነገር ግን ይህ የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ከተደረገ በኋላ ኃይለኛ ምልክቶችን ይከላከላል።

በአሎ (ALLO) ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ውስጥ ታካሚው የግንድ ሕዋሶች (ስቴም ሴሎች) ከለጋሽ ወይም ከእምብርት ደም ከተቀበለ በኋላ በሰውነት ውስጥ ያሉት ሕዋሶች ከውጭ ሕዋሶች ጋር ስለሚዋጉ በጂ.ቪ.ኤች.ዲ (GVHD) የመያዝ አደጋ አለ። ምንም እንኳን ዶክተሮች ለጋሽ ግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ከመውሰዱ በፊት ከታካሚው ጋር መመሳሰልን ቢያረጋግጡም ይህ ከንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) በኋላ ወዲያውኑ ወይም ከአንድ አመት በኋላ ሊከሰት ይችላል።

ታካሚው በዚህ ችግር የሚሰቃይ ከሆነ የረጅም ጊዜ መድሃኒቶች ምልክቶቹን ለመቆጣጠር ይረዳሉ።
ግንድ ሕዋሶች (ስቴም ሴሎች) ከሌሉ ሰውነት ደምን እና የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን ለመስራት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች ማምረት አይችልም። በግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ጊዜ ሰውነት ከጤናማ የስቴም ሴሎች ጋር በመዋሃድ “ይድናል”።

ትክክለኛውን የግንድ ሕዋሶች (ስቴም ሴሎች) መምረጥ ውስብስብ ቢሆንም ሐኪሙ የትኛውን ስቴም ሴሎች የመሰብሰብ ዘዴ ለህክምና ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ይወስናል።

The post የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት (ስቴም ሴል) እንዴት ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/09/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%89%85%e1%8a%92-%e1%8a%95%e1%89%85%e1%88%88-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8b-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%9d-%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%8a%95%e1%88%b5/feed/ 0
በታይላንድ ውስጥ የልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ዳሰሳ https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%89%a0%e1%89%b3%e1%8b%ad%e1%88%8b%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%8d%e1%89%a5-%e1%89%a7%e1%8a%95%e1%89%a7-%e1%89%ab%e1%88%8d%e1%89%ad-%e1%88%9d%e1%89%b5%e1%8a%ad/ https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%89%a0%e1%89%b3%e1%8b%ad%e1%88%8b%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%8d%e1%89%a5-%e1%89%a7%e1%8a%95%e1%89%a7-%e1%89%ab%e1%88%8d%e1%89%ad-%e1%88%9d%e1%89%b5%e1%8a%ad/#respond Mon, 24 Apr 2023 02:56:32 +0000 https://www.vejthani.com/?p=29420 የልብ ቧንቧዎችን ለመተካት ወይም ለመጠገን የሚደረግ ቀዶ ጥገና አሁን በዓለም ዙሪያ በየቀኑ ወደመከናወን ደረጃ ደርሷል። በታይላንድ ውስጥ በቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ሙያ ከተካኑ ሆስፒታሎች አንዱ ባንኮክ የሚገኘው ቬጅታኒ ሆስፒታል ነው።

The post በታይላንድ ውስጥ የልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ዳሰሳ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

የልብ ቧንቧዎችን ለመተካት ወይም ለመጠገን የሚደረግ ቀዶ ጥገና አሁን በዓለም ዙሪያ በየቀኑ ወደመከናወን ደረጃ ደርሷል። በታይላንድ ውስጥ በቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ሙያ ከተካኑ ሆስፒታሎች አንዱ ባንኮክ የሚገኘው ቬጅታኒ ሆስፒታል ነው።

በልብ ውስጥ የሚፈሰውን ደም የሚቆጣጠሩት የልብ ቧንቧዎች ጠርዝ በደንብ ካልተዘጋ እና ደም ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንዲፈስ ሲፈቅድ ወይም የልብ ቫልቭ ስቴኖሲስ ሲከሰት የቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋል።

በቬጅታኒ ሆስፒታል ውስጥ ባሉት የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ሙያዊ እውቀት እና ችሎታ አማካኝነት ቀዶ ጥገናው በከፍተኛ የደህንነት ደረጃ ይከናወናል። ይህ ቀዶ ጥገና የታካሚዎችን ህይወት ለማራዘም እና የተሻለ የህይወት ጥራት እንዲኖራቸው ምክንያት ነው።

ሶስቱ ዋና ዋና የቧንቧ (ቫልቭ) መተካት ዘዴዎች ቲኤቪአይ (TAVI), ኤምአይኤስ (MIS) እና ክፍት የልብ ቀዶ ጥገና ናቸው። በተጨማሪም አራተኛ አማራጭ ሲኖር እሱም የቧንቧ (ቫልቭ) ጥገና ቀዶ ጥገና ይባላል። ጥገናው የበለጠ አዋጭ የሚሆንባቸው የተወሰኑ ሁኔታዎች ሲኖሩ እነዚህም የልብ ቧንቧ (ቫልቭ) በጥሩ ሁኔታ ላይ ካለ ወይም የቧንቧ (ቫልቭ) መጥበብ ችግር በሚፈጠርበት ጊዜ ነው።

በቴክኒክ እድገቶች በመታገዙ የልብ ቀዶ ጥገና ለታካሚው ደህንነቱን የተጠበቀ እና ለቀዶ ጥገና ሐኪሞችም ይበልጥ መደበኛ እየሆነ መጥቷል። እነዚህ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች አሁን ከእነዚህ ሶስት የመተካት ሂደት አማራጮች መካከል አንዱን መምረጥ ይችላሉ ፣ ይህም ማለት አሰራሩን ከታካሚው ሁኔታ ጋር እንዲስማማ በቅርበት ማበጀት ፣ የበለጠ ምቹ ውጤትን ማረጋገጥ ፣ ታካሚውን ከማገገም በተጨማሪ የበለጠ ምቾት እንዲሰማው ማድረግ እናም ታካሚዎች ወደ መደበኛ አኗኗራቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ መመለስ እንዲችሉ ያደርጋል።

ክፍት ቀዶ ጥገና

በፊልሞች ውስጥ ብዙውን ጊዜ የሚታየው ይህ ዓይነቱ የቀዶ ጥገና ዘዴ ነው። በደረት ውስጥ አንድ ትልቅ ቀዶ ጥገና ይደረጋል፣ እና በደረት አጥንት በኩል የጎድን አጥንቶች ወደ ኋላ በመመለሻዎች ይሳባሉ፣ እና የአሰራር ሂደቱን ለማከናወን እንዲቻል ልብ ይጋለጣል።

የታካሚውን የተፈጥሮ ቧንቧ (ቫልቭ) ለመተካት ዲስኮችን የሚመስሉ ሰው ሰራሽ ቧንቧዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ። እነዚህ ቧንቧዎች ወደ ልብ ውስጥ በሚገባ ደምን እያጣራ የሚያሰራጭ የልብ ክፍል (ቬንትሪክል) መጨረሻ ላይ ይጣበቃሉ። በእነሱ ውስጥ የሚፈሰው የደም መፍሰስ ተግባር የአዲሶቹን ቧንቧዎች መከፈትና መዘጋት ይቆጣጠራል።

ክፍት ቀዶ ጥገና እንደተለምዶው ከቀዶ ጥገናው በኋላ በሆስፒታል ውስጥ የአንድ ሳምንት ቆይታ እና በአጠቃላይ ከስምንት እስከ አስራ ሁለት ሳምንታት አካባቢ የማገገሚያ ጊዜ ያስፈልገዋል።

ትራንስካቴተር አኦርቲክ ቫልቭ ኢምፕላንቴሽን (ቲኤቪአይ)

ቲኤቪአይ (TAVI) ቀጭን ካቴተር ወይም ቱቦ በሰውነት ውስጥ ባለው የደም ቧንቧ ውስጥ በተለይም በላይኛው እግር ወይም በደረት ውስጥ ማስገባትን ያካትታል። ካቴቴሩ ወደ ወሳጅ ቧንቧ እንዲገባ ይደረጋል፣ እዚያም ተፈጥሯዊውን

የሚተካ ሰው ሰራሽ ቧንቧ (ቫልቭ) ለመምራት እና ለመጠገን ያገለግላል።

ቲኤቪአይን መምረጥ ጥቅሞች አሉት፣ ልብን ማስቆም ስለማያስፈልግ ታካሚውን በልብ-ሳንባ ማለፊያ መሳሪያ ላይ ማድረግ አያሻም። እናም አሰራሩ በደረት ላይ ትልቅ መቀደድን ፣ ከዛም ጋር ተያይዞ የሚመጣ የህዋስ ጉዳት እና ረጅም የሆነ የማገገምያ ምዕራፍ አያኖረውም።

ክፍት የልብ ቀዶ ጥገናን ለማድረግ አስጊ ሲሆን ነገር ግን ቧንቧ (ቫልቭ) መተካት የግድ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች በሚኖሩ ጊዜ ቲኤቪአይ (TAVI) የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ምርጫ ነው።

ሚኒማሊ ኢንቬሲቭ ቀዶ ጥገና (ኤምአይኤስ)

ኤምአይኤስ ቀዶ ጥገና የሚካሄደው እንደ ክፍት የልብ ቀዶ ጥገና ሳይሆን ፣ በደረት በቀኝ በኩል ወደ ልብ ለመድረስ በጎድን አጥንት በኩል ብዙ ትናንሽ ቀዳዳዎችን በማድረግ ነው። ኤምአይኤስን በቀዶ ሕክምና ሐኪሞችም ሆነ በታካሚዎቻቸው ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን የሚያደርጉት ብዙ ጥቅሞች አሉት።

ቁስሎቹ ያነሱ ስለሆኑ በኤምአይኤስ ቀዶ ጥገና ወቅት የሚኖረው የደም መፍሰስ ከክፍት ቀዶ ጥገና አንፃር ያነሰ ስለሆነ አነስተኛ የደም ምትክ ያስፈልገዋል። ትንሽ ቀዳዳ መሆኑ ደግሞ የመበከል እድሉን ስለሚቀንስ በአካባቢው ሕብረ ሕዋሳት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ያነሰ ይሆናል በተጨማሪም ታካሚው ሲያገግም ሊኖር የሚችለውን ህመም ይቀንሳል። ይህም በሆስፒታሉ ውስጥ አጭር ቆይታን ፣ በአጠቃላይ ፈጣን ማገገምን ፣ የታካሚውን መደበኛ እንቅስቃሴዎች እና የአኗኗር ዘይቤዎች በፍጥነት መመለስን ያመለክታል። እንዲሁም በደረት ላይ የሚኖሩ ጠባሳዎች እምብዛም የማይታዩ ይሆናሉ ማለት ነው።

ቧንቧ (ቫልቭ) ጥገና አማራጭ

ምንጊዜም በተቻለ መጠን የታካሚውን ነባር የልብ ሕብረ ሕዋስ መጠገን ተቀዳሚ ምርጫ ነው።

ለልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ቀዶ ጥገና ቬጅታኒ ሆስፒታልን ያነጋግሩ

ለልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ እና ጥገናን ለማድረግ ሶስት ዘዴዎች ሲኖሩ ባንኮክ የሚገኘው ቬጅታኒ ሆስፒታል የልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ቀዶ ጥገና ከሚያከናውኑ ከፍተኛ የህክምና ተቋማት አንዱ ነው። ከዶክተር ጋር የምክክር ክፍለ ጊዜ ለማስያዝ ቬጅታኒ ሆስፒታልን ያነጋግሩ።

The post በታይላንድ ውስጥ የልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ዳሰሳ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%89%a0%e1%89%b3%e1%8b%ad%e1%88%8b%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%8d%e1%89%a5-%e1%89%a7%e1%8a%95%e1%89%a7-%e1%89%ab%e1%88%8d%e1%89%ad-%e1%88%9d%e1%89%b5%e1%8a%ad/feed/ 0
የማዕድን እጥረት የበሽታ ስጋትን ከፍ ሊያደርግ ይችላል – የነገ ጤናዎን ለማረጋገጥ ኦሊጎስካን ያድርጉ https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a5%e1%8c%a5%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%a0%e1%88%bd%e1%89%b3-%e1%88%b5%e1%8c%8b%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%8d%8d-%e1%88%8a%e1%8b%ab/ https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a5%e1%8c%a5%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%a0%e1%88%bd%e1%89%b3-%e1%88%b5%e1%8c%8b%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%8d%8d-%e1%88%8a%e1%8b%ab/#respond Thu, 20 Apr 2023 04:33:13 +0000 https://www.vejthani.com/?p=29398 የማዕድን እጥረት እንዴት የበሽታ ስጋትን እንደሚያሳድግ እና
ጤናዎን በኦሊጎስካን የማዕድን ደረጃ ማጣሪያ ምርመራ እንዴት
እንደሚቆጣጠሩ ይወቁ። የማዕድን ሚዛን አለመመጣጠንን
በመለየት የወደፊት ጤናዎን ይጠብቁ ።

The post የማዕድን እጥረት የበሽታ ስጋትን ከፍ ሊያደርግ ይችላል – የነገ ጤናዎን ለማረጋገጥ ኦሊጎስካን ያድርጉ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

Vitamin and mineral deficiencies might be the cause of several diseases. Vitamin A is associated with our vision. Vitamin B1 deficiency leads to Beriberi (numbness in the hands and feet), while a lack of vitamin B2 may cause a canker sore. Low levels of iron in the body might result in anemia. A phosphorus deficiency could cause bladder stones, and if a patient has a goiter, it might result from iodine deficiency.   

Apart from these, high levels of heavy metals in the body, such as aluminum, arsenic, mercury, lead, and cadmium which are commonly-found chemicals in everyday life, may cause fatigue, disorientation, and sluggishness.

Currently, a cutting-edge technology called “OligoScan” is used to assess the concentration of heavy metals and minerals in the body. The device is held over 4 points of the palm to record the wavelengths of minerals in the tissues. OligoScan indicates:

  • Levels of 15 types of heavy metals in the body 
  • Levels of 21 types of minerals in the body
  • Levels of essential vitamins in the body

OligoScan screening test takes around 2-3 minutes. It is a painless and non-invasive method done without a blood specimen. The test gives instant results and is more precise than a standard blood test as it has an in-depth measuring system.

For more information, please contact

Vejthani Q-Life Center, 11th Floor, Vejthani Hospital
Tel. 02-734-0000 Ext. 1125, 1126
or +66 (0) 85-223-8888 (English Hotline)

The post የማዕድን እጥረት የበሽታ ስጋትን ከፍ ሊያደርግ ይችላል – የነገ ጤናዎን ለማረጋገጥ ኦሊጎስካን ያድርጉ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a5%e1%8c%a5%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%a0%e1%88%bd%e1%89%b3-%e1%88%b5%e1%8c%8b%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%8d%8d-%e1%88%8a%e1%8b%ab/feed/ 0
የካንሰርን ዋና መንስኤ ከፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ህክምና ያግኙ እና ያክሙ https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%8b%a8%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad%e1%8a%95-%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%88%b5%e1%8a%a4-%e1%8a%a8%e1%8d%95%e1%88%a8%e1%88%b2%e1%8b%a5%e1%8a%95-%e1%89%b5%e1%8a%ad%e1%8a%ad/ https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%8b%a8%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad%e1%8a%95-%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%88%b5%e1%8a%a4-%e1%8a%a8%e1%8d%95%e1%88%a8%e1%88%b2%e1%8b%a5%e1%8a%95-%e1%89%b5%e1%8a%ad%e1%8a%ad/#respond Tue, 11 Apr 2023 08:36:57 +0000 https://www.vejthani.com/?p=29309 በ2021 በተደረገ ጥናት 139,206 አዲስ የካንሰር ታማሚዎች እንደነበሩ እና ከነዚህም ውስጥ 84,073ቱ ሞተው እንደነበር ከብሄራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ አረጋግጧል። በታይላንድ ውስጥ በጣም ተስፋፍተው የሚገኙ አምስት የካንሰር ዓይነቶች የጉበት እና የሃሞት ቱቦ ካንሰር፣ የጡት ካንሰር፣ የሳንባ ካንሰር እና የአንጀት እና የፊንጢጣ ካንሰር እንዲሁም የማህፀን በር ካንሰር ናቸው። የካንሰር ሕክምና በአሁኑ ጊዜ በማጣሪያ ቴክኖሎጂዎች እና የኬሞቴራፒ ሕክምናዎች በመታገዝ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለመቀነስ እና ለእያንዳንዱ በሽተኛ ግላዊ የሕክምና ለማቀድ የተዘጋጁ ናቸው።

The post የካንሰርን ዋና መንስኤ ከፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ህክምና ያግኙ እና ያክሙ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>

በ2021 በተደረገ ጥናት 139,206 አዲስ የካንሰር ታማሚዎች እንደነበሩ እና ከነዚህም ውስጥ 84,073ቱ ሞተው እንደነበር ከብሄራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ አረጋግጧል። በታይላንድ ውስጥ በጣም ተስፋፍተው የሚገኙ አምስት የካንሰር ዓይነቶች የጉበት እና የሃሞት ቱቦ ካንሰር፣ የጡት ካንሰር፣ የሳንባ ካንሰር እና የአንጀት እና የፊንጢጣ ካንሰር እንዲሁም የማህፀን በር ካንሰር ናቸው። የካንሰር ሕክምና በአሁኑ ጊዜ በማጣሪያ ቴክኖሎጂዎች እና የኬሞቴራፒ ሕክምናዎች በመታገዝ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለመቀነስ እና ለእያንዳንዱ በሽተኛ ግላዊ የሕክምና ለማቀድ የተዘጋጁ ናቸው።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የካንሰር ሕክምና ኦንኮሎጂስት የሆኑት ዶክተር ቪግሮም ጄኔቲሲን እንደተናገሩት ከሆነ ስለ ካንሰር ሕክምና በጣም አስፈላጊው ነገር በእያንዳንዱ ታካሚ ውስጥ የካንሰርን መንስኤ ማግኘት ነው። መንስኤውን በካንሰር ሕዋሳት ላይ የማጣሪያ ምርመራ በማካሄድ ሴሎቹ በምን አይነት ዘዴ ወደ ካንሰርነት እንዲቀየሩ ያደረጋቸው እንደሆነ ለማወቅ እና በእያንዳንዱ ታካሚ ላይ የካንሰርን እድገት ለመግታት ምርጡ መድሃኒት ምን እንደሆነ በመመርመር ሊገኝ ይችላል። ስለዚህ ህክምናው የበለጠ ትክክለኛ እና ውጤታማ ሊሆን ይችላል። የዚህ ዓይነቱ የሕክምና ዘዴ ፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ሕክምና ተብሎ ይጠራል። ይህ የሆነበት ምክንያት የተለያዩ ዘዴዎች በአንድ አካል ውስጥ የካንሰር እድገትን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ነው።

ዶ/ር ቪግሮም አክለውም ይህ ፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ሕክምና የካንሰር ህዋሶችን የመመርመር እና የመተንተን ሂደት ሲሆን ይህም የካንሰር አይነት፣ ደረጃ እና ገጽታ ብቻ ሳይሆን ዝርዝር መረጃን ጭምር ያሳያል። የዚህ ዓይነቱ ሕክምና ሴሎችን ወደ ዘረ መል (ዲ ኤን ኤ) ውስጥ በጥልቀት ይመረምራል። ይህም በታካሚ ላይ የደም ምርመራ ወይም ባዮፕሲ በማድረግ የተሰበሰበውን ደም ወይም ቲሹን ለመተንተን በቤተ ሙከራ ውስጥ በመላክ የተማከለው ትልቅ መረጃ (Big Data) ነው። ይህ ከሰው ወደ ሰው የሚለየውን የበሽታው መንስኤ እንዴት እንደሚከሰት ለማወቅ ይረዳል። ይህም ሐኪሙ ለእያንዳንዱ በሽተኛ እጅግ ተስማሚ የሆነውን መድሃኒት እንዲመርጥ ያስችለዋል እናም ከመጀመሪያው ደረጃ ጀምሮ አላስፈላጊ ወይም የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን መጠቀምን ያስችላል።

“ይህ ፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ህክምና በጂኖም ሴኪውሲንግ ማሽን ከታካሚው በተገኘው የካንሰር ሕዋሳት ውስጥ ያለውን የዘረ መል (ዲ ኤን ኤ) ትንተና ይጠይቃል። ዓላማው ከትልቅ መረጃ (Big Data) ጋር የንፅፅር መረጃ (comparative data) ትንተና ከማድረጉ በፊት የጂን ሚውቴሽንን ጨምሮ ማናቸውንም ያልተለመዱ ነገሮችን በደንብ መፈለግ ነው። ይህ በሽተኛው በካንሰር ሕዋሳት ውስጥ ምን ዓይነት ያልተለመዱ ሁኔታዎች እንዳሉ እና የትኛው የሕክምና ዘዴ የተሻለውን ውጤት እንደሚያሳይ ለማወቅ ያስችለናል። በተጨማሪም የታካሚውን ሥር የሰደደ በሽታ, ጭንቀታቸውን እና ገደቦችን ግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። ለምሳሌ፣ አንዳንድ ሕመምተኞች የፀጉር መርገፍን ይፈሩ ይሆናል፣ ስለዚህ ለዚህ ሕመምተኛ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ውጤታማ ሕክምናን እናስብ ይሆናል። ይህ ፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ህክምና በእውነት በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ ሕክምና ያደርገዋል።”

ዶ/ር ቪግሮም አክለውም ዶክተሩ የካንሰርን ዋና መንስኤ በፕረሲዥን የካንሰር ህክምና (Precision Cancer Medicine) ሲያውቅ የህክምና እቅዱን የበለጠ ግላዊ እና ውጤታማ ያደርገዋል። የሕክምና ዘዴዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  1. ታርጌትድ ቴራፒ (Targeted Therapy): በእያንዳንዱ ታካሚ ውስጥ የካንሰር እድገትን የሚያመጣው ዘዴ ትንተና የትኛው የጂን ሚውቴሽን መደበኛ ሴሎችን ወደ ካንሰር እንደሚያነሳሳ ለማወቅ ያስችላል። ይህ ዶክተሮች በሽታውን የሚያመጣውን ልዩ ዘዴ ለማጥቃት የታለሙ መድኃኒቶችን በትክክል እንዲመርጡ ያስችላቸዋል ፣ ይህም በመደበኛ ሕዋሳት ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ ትክክለኛ የካንሰር ሕክምናን ያስገኛል ፣ ምክንያቱም የተሰጡት መድኃኒቶች በተወሰነ ቦታ ላይ ብቻ ምላሽ ስለሚሰጡ እና የካንሰር ሕዋሳት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ። ያልተለመዱ የጂኖም መገለጫዎች አሏቸው። ይህ ህክምናው በጣም ውጤታማ እንዲሆን እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊቀንስ ይችላል።
  2. ኢሚውኖ ቴራፒ (Immunotherapy): ይህ የካንሰር ሕዋሳትን እድገት ወይም መስፋፋት የሚቀሰቅሰው ጠቃሚ ዘዴ የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳትን በመለየት እና የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳትን ተግባር በመከልከል ነው። ይህ የበሽታ መከላከያ ሴሎች የካንሰር ሕዋሳትን ለማጥፋት እንዳይችሉ ያደርጋል። ኢሚውኖ ቴራፒ (Immunotherapy) የካንሰር ሕዋሳትን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስወገድ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት መቀየርያን እንደ ማብራት ነው። ፕረሲዥን የካንሰር ህክምና (Precision Cancer Medicine) በካንሰር ሕዋሳት እና በሽታ ተከላካይ ሕዋሶች ውስጥ አመላካቾችን በመለየት ምላሻቸውን ለመተንበይ እና ለእያንዳንዱ በሽተኛ ምርጡን የበሽታ መከላከያ መድሃኒቶችን እንዲመርጥ ስለሚረዳ የትኞቹ ታካሚዎች ለበሽታ ህክምና ተስማሚ እንደሆኑ ይወስናል።
  3. ሆርሞናል ቴራፒ (Hormonal Therapy): ሆርሞናል ቴራፒ የጾታ ሆርሞኖችን ተግባር ወይም ምርትን ለመግታት መድሃኒቶችን መጠቀም ነው። ይህ በጾታዊ ሆርሞኖች የሚቀሰቀሰውን የካንሰር ሕዋሳት እድገት ሊገታ ይችላል። ይህ ከካንሰር መንስኤ ጋር የሚጣጣሙ መድሃኒቶችን በትክክል መጠቀሙ ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ የፕረሲዥን ካንሰር ህክምና መድሃኒት አይነት ነው። አሁን ላይ ይህ ህክምና በወንዶች ላይ የፕሮስቴት ካንሰርን እና በሴቶች ላይ የጡት ካንሰርን ለማከም በሰፊው ጥቅም ላይ ውሏል።
  4. ኪሞቴራፒ (Chemotherapy): በፕረሲዥን የካንሰር ህክምና (Precision Cancer Medicine) ውስጥ ኪሞቴራፒ የሚሰጠው ዶክተር ለእያንዳንዱ በሽተኛ ለካንሰር በጣም ተስማሚ የሆነውን መድሃኒት በመምረጥ በመረጃው ላይ ተመርኩዞ ካንሰር ጄኖሚክ ፕሮፋይሎች እና ከካንሰር አምሳያ ጋር በመመርመር በታካሚው ውስጥ መድሃኒቱን ከመጠቀም በፊት በቤተ ሙከራ ውስጥ ላለው እያንዳንዱ ዓይነት ኬሞቴራፒ እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ ለመገምገም ነው። የኬሞቴራፒ ሕክምናን የመጠቀም አስፈላጊው መርህ ለታካሚዎች ብቻ የሚጠቅመውን የኬሞቴራፒ ዓይነት መወሰን ሲሆን ኪሞቴራፒ በታካሚው ውስጥ የሕክምናውን ውጤታማነት ካላሳደገው እሱ / እሷ የኬሞቴራፒ ሕክምና አያስፈልጋቸውም። ይህ የሕክምናውን ውጤታማነት ሳይቀንስ አላስፈላጊ የጎንዮሽ ጉዳቶችን እድል ለመቀነስ ይረዳል።
  5. ሴል ቴራፒ (Cell therapy): በአሁኑ ጊዜ የካንሰር ሕዋሳትን ለማስወገድ ሚና የሚጫወቱትን በበሽታ የመከላከል ስርዓት ውስጥ የታካሚውን ሕዋሳት ማጠናከር እንችላለን። ሕክምናው በካንሰር ዓይነት እና በታካሚው የጤና ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ እንደ ጤናማ ሕዋሳት እጥረት ወይም ዝቅተኛ ጥራት ያለው ሕዋሳት መጠን ሊስተካከል ይችላል፣ የሕዋስ ሕክምናም በእንደ እነዚህ አይነት ምክንያቶች ይለያያል። የተጠናከሩት የበሽታ መከላከያ ህዋሶች በእያንዳንዱ በሽተኛ የካንሰር አይነት እና ደረጃ ላይ በመለየት መመረጥ አለባቸው።

ፕረሲዥን የካንሰር ህክምና (Precision Cancer Medicine) ለካንሰር በሽተኞች አዲስ አማራጭ ሲሆን ካንሰርን ከመሰረቱ ላይ የሚያክም እና ግላዊ የሆነ የህክምና ውጤት ይሰጣል እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳቶችን እድል ይቀንሳል።

The post የካንሰርን ዋና መንስኤ ከፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ህክምና ያግኙ እና ያክሙ appeared first on Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand..

]]>
https://www.vejthani.com/am/2023/04/%e1%8b%a8%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%88%b0%e1%88%ad%e1%8a%95-%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%88%b5%e1%8a%a4-%e1%8a%a8%e1%8d%95%e1%88%a8%e1%88%b2%e1%8b%a5%e1%8a%95-%e1%89%b5%e1%8a%ad%e1%8a%ad/feed/ 0